No comments yet

የዮሐንስ መጽሐፍ

እኔ ስሜ ዮሐንስ ተሾመ ነው የሚባለው እ በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ክልል
ጽ/ቤት ትምህርት ቤት ውስጥ በአስተባባሪነት ነው የማገለግለው ከዚያም በተጨማሪ የተለያዩ ትምህርት
ቤቶች ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስን አስተምራለሁ፡፡ ስሜ ዮሐንስ ተሾመ ይባላል በመሠረተ ክርስቶስ
ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ክልል ጽ/ቤት ውስጥ በትምህርት ዘርፍ አስተባባሪነት ነው የማገለግለው፡፡ እሽ
ስሜ ዮሐንስ ተሾመ ይባላል በአዲስ አበባ ክልል በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ትምህርት ዘርፍ ውስጥ
ነው የማገለግለው እ እንደ አጋጣሚ ሆኖ የአዳምሰገድን መጽሐፍ አንብቤ አንዳንድ ነገሮችን ለማየት
ሞክሬያለሁ ከዚህ አኳያ ያገኘኋቸውን ጥሩ ነገሮችና ስለ መጽሐፉ ኮሜንት ለማድረግ ነው እዚህ የተገኘሁት፡፡
ከእዚህ ጋር በተገናኘ በቤተክርስቲያን ያሉ ወጣቶች ማንበብ ጋር በተገናኘ ተነስቼ አንዳንድ ነገሮች ባወራ
ዘመናችን አሁን እኛ ያለንበት ዘመን በጣም ከእምነታችን አኳያ በጣም ምክንያታዊና ጠርጣራነትን ማራመድ
ያለብን ጊዜ ውስጥ ነው ያለነው ማለት የምንሰማውን የምናየውን ሁሉ የምንቀበልበት ጊዜ ውስጥ አይደለም
ያለነው በዚህ ዘመን ውስጥ እንዳለ ወጣት የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትንም ሆነ የመናገኛቸው መጽሐፍቶችን
የምንሰማቸው ነገሮችን ስንሰማ በጣም አጽንኦት ባለበት ሁኔታ መስማታችን በጣም አስፈላጊ ነው ከዚህ ጋር
በተገናኘ እንግዲህ ወጣቱ በጣም በብዙ ሚዲያዎች ብዙ ነገር የሚሰማበት ጊዜ ነው ተደራሽነቱ በጣም ቅርብ
የሆነበት ዘመን ውስጥ ነው ያለነው ይሄ ዘመን ስለዚህ የሚሰማውንም የሚያየውንም ነገር በትክክለኛ
የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ውስጥ ለማቆየት ወጣት የግድ የዚህ ዘመን ወጣት የማንበብ ባህልን ማሳደጉ
በጣም ዋናና አስፈላጊ ነገር ነው፡፡

ይሄ የሚሆንበት ምክንያት ምንድነው መጽሐፍ ቅዱስ የሚነበብ ብቻ ሳይሆን በዋናነት የሚጠናም
መጽሐፍ ነው መጽሐፍ ቅዱስ መጠናት አለበት፡፡ እ ሰዎች የሚነግሩንን ብቻ፣ ሰባኪዎች የሚነግሩንን ብቻ
ወይም እኛ ዝም ብለን ጠዋት ላይ ወይም ማታ ላይ የምናነባትን ብቻ ሳይሆን መጽሐፍቶችን ጊዜ ሰጥተን
ልናጠና የራሳችን የሆነ በመንፈስ ቅዱስ ውስጥ የሆነ መረዳት ልናገኝ የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው፡፡ ይሄን
ለማድረግ ደግሞ እንደዬ አቅማችን መጽሐፍ ቅዱሶችን ለመረዳት የሚያብራሩ መጽሐፍቶችን ማግኘት ደግሞ
በጣም በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ በእኛ አገር በአማርኛ ቋንቋዎች የተሠሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያዎች
የማግኘት ነገር ብዙ ሰፊ አይደለም፡፡ ጠባብ ነው ያለው ከዚህ ጋር በተገናኘ እንግዲህ ወንድማችን አዲያምሰገድ
መጽሐፍቶችን እያበረከተ ነው ያለው እኔ በአጋጣሚ እሱ ከሠራቸው መጽሐፍቶች ብዙ መጽሐፍትን እንደሠራ
ሰምቻለሁ፡፡ ከሠራቸው መጽሐፍቶች አንዱን መጽሐፍ ማግኘት ችያለሁ የዮሐንስ ወንጌል ላይ የተሠራ ኮመንታሪ
መጽሐፍ አግኝቼ መጽሐፉን ለማየት ሞክሬያሁ፡፡ በእውነት በዚህ ዘመን ጊዜ ሰጥቶ ብዙ መጽሐፍትን አገላብጦ
የመጽሐፍን ነገር አደራጅቶ መጻፍ ትልቅ ትልቅ ችሎታ ነው እና በዚህ አኳያ ወንድማችን በጣም ሊመሰገን፣
ሊበረታታ የሚገባበት ጊዜ ነው ምንድነው መጽሐፍቶችን ስናገኝ እንደዚህ ዓይነት መጽሐፍቶች ማበረታታት
የተሻለ ሥራ እንዲሠሩ የማበረታታት ነገር በጣም አስፈላጊ ነው አቅም ካለ ደግሞ እነሱ ከተነሱበት ነገር
ተነስተን የተሻሉ ነገሮችን ለመሥራት ኮንትሪቢውት ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ እና ከዚህ ጋር በተገናኘ ወንድማችን
የሠራውን ይሄንን መጽሐፍ በጣም እንድናነበው እንድንጠቀም እኔ ኢንኬሬጅ አደርጋለሁ ወንድማችንም በዚህ
ሥራ እንዲበረታ አሳስባለሁ በጣም ጥሩ ሥራ እንደሠራ አይቻለሁ፡፡

ከመጽሐፉ ጋር በተገናኘ መጽሐፉን ሙሉ ለሙሉ ሃያ አንዱንም ምዕራፍ ባላይም ግን በጣም ወሳኝ
የሆኑትን ጥሩ ጥሩ ነገሮችን ለማየት ሞክሬያለሁ መጽሐፉ በእውነት ቤተክርስቲያን ውስጥ ላለ አገልግሎት፣
ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ዮሐንስ መጽሐፍን ለማጥናት ለሚፈልጉ ሰዎች በጣም የሚጠቅም ጥሩ መጽሐፍ
ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ መጽሐፉ አንደኛ ባክግራውንድ ይሰጣል እኔ እንዳየሁት እንዳነበብኩት ከሆነ ስለእያንዳንዱ
ክፍል የእያንዳንዱ ክፍል የሐሳብ ፍሰት ጠብቆ፣ በሐሳብ ፍሰት ውስጥ ያሉትን ባክግራውንድ ሰጥቶ
ከባክግራውንድ ባለፈ ደግሞ ክፍሎቹን ኤክስጁዌት አድርጎ ማለፍ ትንሽ አብራርቶ ከፈት አድርጎ ለማሳየት
የሞከረ መጽሐፍ ነው፡፡ ዮሐንስን ለማጥናት ለቁም መሰለኝ እኔ እኔ አድርጌዋለሁ፡፡

እንግዲህ መጽሐፉን እንደ ለማንበብ ሞክሬያለሁ በተወሰነ መጠን መጽሐፍቱን አንብቤያቼዋለሁ፡፡
የመጽሐፍቱ አቀራረብ እኔ በጣም ተመችቶኛል፡፡ አንደኛ መጽሐፍቱ ላይ ባሉት ትውፊታዊ ትረካው ውስጥ ባሉት
የሐሳብ ፍሰቶችን በመጠበቅ የዚያን ሐሳብ ፍሰት ታሪካዊ ዳራውን በማሳየት ባክግራውንዱን በማሳየት እዚያ
ውስጥ ያሉትን ታሪካዊ ነገሮችን በማብራራት የመጽሐፍ ቅዱስ ሌሎች ክፍሎችን ከብሉ ኪዳን ሊሆን ይችላል
ከተጓዳኝ የአዲስ ኪዳን ሊሆን ይችላል አገናኝቶ በማስቀመጥ ከዚያ በተረፈ ደግሞ ክፍሉን እራሱን ደግሞ
እዚያው ክፍል ላይ ሊባል የተፈለገውን፣ ሊተላለፍ የተፈለገውን መልዕክት በማብራራት በጣም በቀላልና
ማንኛውም ሰው አንብቦ ሊረዳው በሚችለው መንገድ የቀረበ መጽሐፍ እንደሆነ አግኝቼዋለሁ እና በየትኛውም
ትንንሽ መጽሐፍት ጥናቶች ውስጥ በግል በሆነ ጥናት ሰፋ ባለም ግሩፖች ውስጥ ቢጠና በጣም ጥሩ የሆነ
ለብዙዎች መጥቀም የሚችል ኢቭን ትምህርት ቤት ያሉ ተማሪዎች ክፍሉ ላይ ያሉ ባክግራውንድ ክፍሎችን
መረጃዎችን ሊያገኙበት የሚችሉበት መጽሐፍ እንደሆነ አይቻለሁና በጣም ጊዜ ተፈጅቶ በጣም በጥሩ ሁኔታ
የተሠራ እንደሆነ አይቻለሁ፡፡ ከዚያ አኳያ እንግዲህ ወጣቶች ስብከትም ቢሰሙ፣ ትምህርትም ቢሰሙ ስፔሻሊ
አሁን በእጃችን የገባው ከዮሐንስ ወንጌል ጋራ ቤታቸው ገብተው እንደ ሪፈረንስ ቢጠቀሙበት የተባለውን ነገር
ለማገናዘብ ለመመልከት የሚረዳ ትንሽ ብርሃን የሚሰጥ መጽሐፍ እንደሆነ አይቻለሁና ወጣቶችም ሌሎችም
ሰዎች እንዲያነቡት ኢንኬሬጅ አደርጋለሁ አመሰግናለሁ፡፡ አይዶኖ የምጨምረው ነገር ካለኝ አላውቅም፡፡

 

 

አስተያየት ለጥፍ