አዲያምሰገድ በጻፈው መጽሐፍ መሠረት እ ብዙ በኢትዮጵያ ውስጥ የንባብ ልማድ እንደሌለ ይነገራል
እና ያንን ልማድ ለማሳደግ ደግሞ ይሄ ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መጽሐፍ ነው፡፡ በተለይ ወጣቶችን
ደቀመዝሙር ለማድረግ በስፋት የተዘጋጀ መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት ማጥናት እንዳለባቸው የሚያሳይ መጽሐፍ
ነው በዚህ መጽሐፍ ውስጥ በስፋት የመናያቸው ነገሮች የኤፌሶን መጽሐፍ እንደምናውቀው ስድስት ምዕራፍ
ያለው መጽሐፍ ነው ነገር ግን መጽሐፉ በጣም ትልቅ ነው ትልቅነቱ ውስጡ ገብተን ስናነበው እ ከውጭ
እንደምናየው የሚያስፈራ አይደለም ነገር ግን ማንበብ ስንጀምር የምንወደው መጽሐፍ ነው፡፡
የንባብ ልማድን ለማሳደግ ያው መሰጠትን ይጠይቃል እና ብዙ ጊዜ ጊዜያዊ የሆኑ ነገሮች ላይ ጊዜ
ማሳለፍ እንወዳለን፡፡ ነገር ግን የሚያነብ ሰው ብዙ እውቀት ያገኛል እንደገና ደግሞ ዲሲፕሊንም ይጠይቃልና
ሰዎች ሲያነቡ እራሳቸውን ያሳድጋሉ እግዚአብሔርም ለመሰጠት ደግሞ አቅም እንዲኖረን ያደርጋልና የንባብ
ልማዳችንን ለማሳደግ የሚያበረታቱ ነገሮችን ለማድረግ በተለይ ቤተሰብ እያነበበ ወጣቶችን ልጆችን እንዲያነቡ
ማበረታታት ይኖርበታል ብዬ አስባለሁ፡፡ አንዳንድ ጊዜ እኛ ሳናነብ አንብቡ ስንላቸው ልጆች የእኛን ተግባር
ስለሚያዩ ብዙ የሚያነሳሳቸው አይሆንም እና በዚህ ዙሪያ በተለይ ወላጆች በልጆቻችን ፊት እያነበብን እነሱን
ማበረታታት እንዳለብን አስባለሁ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ እነሱን ኢንኬሬጅ ለማድረግ አንብበው ሲጨርሱ እንደ
ስጦታ ሊሆን ይችላል መጋበዝ ሊሆን ይችላል እነዚህን በማድረግ ወደ ንባብ ልምምድ ውስጥ እንዲገቡ
ብናደርጋቸው መልካም ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡
ወንድማችን አዲያምሰገድ በውጭ አገር ባለበት ጫና ይሄንን ትልቅ መጽሐፍ ማዘጋጀት መቻሉ እኔ
መቼም በበኩሌ በጣም አደንቀዋለሁ ምክንያቱም ትንንሽ ጽሑፎችን ለማዘጋጀት መሰጠትን ይጠይቃል ጊዜ
ይጠይቃልና እሱ ካለበት የኑሮ ጫና፣ ውጥረት ሳይዘው ይሄንን የዚህ ዓይነት ለትውልድ የሚጠቅም በአገራችን
ቋንቋ የሆነ መጽሐፍ አዘጋጅቷልና ይሄንን በጣም ላበረታታው እወዳለሁ እንዲያውም ይሄንን ብቻ ሳይሆን ወደ
አሥር የሚሆኑ መጽሐፍትን ጽፏል እኔ ያየሁት የኤፌሶን መጽሐፍ ጥናትን ነው፤ ስለዚህ አሁንም በዚሁ
እንዲቀጥል እላለሁ፡፡ ሌላው ይሄንን መጽሐፍ በተለያየ መንገድ ልንጠቀምበት እንችላለን አንደኛ በቤተሰብ
አምልኮ ላይ እንደ ጥናት መጽሐፍ አድርገን ልንወስደው እንችላለን ወጣቶች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቡድኖች
ላይ በመያዝ ልናጠናበት እንችላለን፡፡ ምክንያቱም ሰፊ የሆነ ሐሳብ ያለው መጽሐፍ ነው፡፡ ብዙ የተሠራበት
እንደሆነ ያስታውቃል ምክንያቱም በውስጡ የታጨቁት ትምህርቶች ከተዘጋጀው ከመጽሐፍ ይቅርታ ይሄንን
እንትን ብትለው ይሻላል ይሄኛውን እንትን ይደረግ እባክህ፡፡ ችግር የለም፡፡
ይሄ በእጄ ላይ የሚገኘው የኤፌሶን ጥናት መጽሐፍ በጣም ሰፊ እውቀትን የሚያስጨብጥ ስለሆነ
በተለይ ወጣቱ አንድ ጊዜ ይሄንን መጽሐፍ ለማጥናት እንደምንም ተበረታተው ቢጎብዙ ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ
ክፍሎችን መጽሐፍትን እንዴት ማጥናት እንዳለባቸው የሚያሳይና ደግሞም የሚያነሳሳ ስፋት መጽሐፍ ቅዱስን
ለማጥናት የሚያነሳሳ መጽሐፍ ነው እንደገና ደግሞ በዚህ መሠረት ሌሎችም ጸሐፊዎች ለትውልዱ
የሚጠቅሙ መጽሐፍትን እንደዚሁ ቢያዘጋጁ የሚያበረታታ ነው እላለሁ፡፡ በአብዛኛው በአገራትን እስከዛሬ
እንጠቀምባቸው የነበሩ መጽሐፍት ትርጉም መጽሐፍትን ነበር ይሄ መጽሐፍ ግን በአማርኛ ቋንቋ መጻፉ ደግሞ
የእኛን አውድ ያገናዘበ ባህላችንን ያገናዘበ በመሆኑ እንዴት ወደ ሕይወት ለመተርጎም እንደምንችል በቀላሉ
የሚያስረዳ መጽሐፍ ነው እላለሁ አመሰግናለሁ፡፡
እሽ አመሰግናለሁ አቤል እሸቱ ድምጼን ከፍ ላድርገው እሽ አቤል እሸቱ እባላለሁ በኢትዮጵያ ቃለ
ሕይወት ቤተክርስቲያን ወጣቶች አገልግሎት ሰብሳቢ ነኝ፡፡ በተጨማሪም ደግሞ የቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን
ሥራ አስፈጻሚ ነኝ፣ አባል ነኝ፡፡ እንግዲህ የአፈበአ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መጽሐፍቶችን የሚያዘጋጀው
አገልግሎት ከዚህ ቀደም የኤፌሶን መልዕክት ጥናትን መጽሐፍ አሳትመዋል፡፡ ይሄንን መጽሐፍ የማየት ዕድል
አለኝ አግኝቻለሁኝ እንግዲህ ከዚህ ጋር ተያይዞ ለወጣቶች እንግዲህ ከዚህ ጋር ተያያዥነት ላላቸው ጉዳዮች
አስተያየቴን ለመስጠት ነው፡፡ እንግዲህ የመጽሐፍቶችን ስናይ ዋናው አገልግሎታቸው ወጣቶችንም ሌሎችንም
ተደራሽ ማድረግ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር የኢትዮጵያ ወጣቶች በተለይ ደግሞ አማኝ ወጣቶች የንባብ ባህላቸውን
በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ እንደሚገባቸው ማሳሰብ እወዳለሁ፡፡ እንደሚታወቅ እኛ ኢትዮጵያውያን ከንባብ ጋር
ብዙ የተቆራኘ ባህል የለንም የንባብ ባህላችን በጣም ደካማ ነው ይሄ ደግሞ በክርስቲያኑ ማኅበረሰብ በተለየ
መልኩ ይጎላል ብዬ አስባለሁኝ፡፡ አብዛኛው ወጣት መጽሐፍ ቅዱስን ምን ያህሉ አንብቦ ጨርሷል ብዬ ትልቅ
ጥያቄ አለኝ ምን ያህሉ ሰው ከዳር እስከ ዳር ቢያንስ አንዴ እንኳን አንብቦ አጠናቋል የሁልጊዜ ጥያቄዬ ነው፡፡
ወጣቶች ደግሞ አሁን ባለው ሁኔታ በርካታ የስህተት ትምህርቶች እየተስፋፉ ያሉበት ሁኔታ ስለሆነ ጊዜ
ትምህርቶች ደግሞ በብዛት ተደራሽ የሚያደርጉት ወጣቱን ስለሆነ ይሄንን ከመከላከል አንፃር ንባብ ባህልን
ማዳበር ተገቢ ነው ብዬ አስባለሁኝ፡፡
እንግዲህ መጽሐፍ ቅዱስን ራሱን የጻፉልን በአንድ ወቅት ወጣት የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ እነ
ጳውሎስንም ብናስብ በአንድ ወቅት ወጣት ነበሩ ሌሎች የብሉ ኪዳን ፀሐፍትንም ስናይ ወጣት ሆነው
የእግዚአብሔርን ሥራ በጽሑፍ ያስቀሩልን ሰዎች ናቸው፡፡ እንግዲህ አንደን የእግዚአብሔርን ሥራ መጽሐፍ
ካልነው ይነበባል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ በተለይ ወጣቶች የንባብ ባህላቸውን በቅጡ ሊያሳድጉ ይገባል ብዬ
እመክራለሁኝ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ሲናገር የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና
ለተግሳጽ በጽድቅ ላለው ምክር እራስንም ለማነጽ እንደሚጠቅም፣ የእግዚአብሔር ሰው ፍጹም እንዲሆን
እንደሚያግዝ ይናገራል፡፡ ጳውሎስም በተለያየ ጊዜ የጻፋቸው መልዕክቶች ላይ እኔ ጳውሎስ በእጄ የጻፍኩት
መልዕክት ይላል ስለዚህ ዞሮ ዞሮ የተጻፈልን መልዕክት ከማንበብ ጋር የተቆራኘ ስለሆነ ወጣቶችን በንባብ
እራሳቸውን እንዲያንጹ፣ በንባብ ራሳቸውን እንዲያጎለብቱ መምከር እፈልጋለሁ፡፡ በተለይ ደግሞ በክርቲያኑ
ሰርክል አካባቢ ብዙ ጸሐፍት እንዳይነሳሱ እንቅፋት ይሆናል ብዬ የማስበው ብንጽፍ አንባቢ እናገኛለን ወይ ብሎ
ብዙ ሰው ጥያቄ አለው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ መጽሐፍ ከታተመ በጣም ትልቅ ስርጭት አለው ቢባል አሥር ሺሕ
አሥራ አምስት ሺሕ መጽሐፍ ነው የሚታተመው በውጩ ዓለም ስናየው በሚሊዮኖች ለዚያውም በተለያየ ዙር
ይታተማሉ ኢትዮጵያ ውስጥ የሕትመት ሥርጭታችንን ስናይ የማንበብ ባህላችን በጣም ደካማ እንደሆነ
እናያለን፡፡ እና አንባቢ ትውልድ ሲፈጠር ጸሐፊ ትውልድም ይፈጠራል ማለት ነው ስለዚህ በዚህ ላበረታታ
እፈልጋለሁኝ፡፡
እንግዲህ ወንደም አዲያምሰገድ የኤፌሶን መልዕክትን ጥናት የሚያግዘን በጣም ደስደናቂ የሆነ
መጽሐፍ ጽፏል መጽሐፉን ለማየት ዕድሉ ነበረኝ፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያየሁት አንድ ትልቅ ነገር ምን ያህል
ይሄ ወንድም ሰፊ ጊዜውን ወስዶ እንደጻፈ አይቻለሁ፡፡ አንደኛ የመጽሐፉ ቮሊዩም ባልተለመደ መልኩ ትልቅ
ነው ከዚያ ባሻገር ደግሞ እያንዳንዱን የኤፌሶን መልክት ፍሬዝ ባይ ፍሬዝ ወይም ደግሞ ሐረግ በሐረግ
የሚተነትን ትንታኔው ደግሞ የእሱን እይታ ብቻ ሳይሆን ሌሎች በኤፌሶን ላይ የተለያዩ መልዕክትን የጻፉ ሰዎች
በእያንዳንዱ መስመር ላይ ያላቸውን ዕይታ ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ለማየት እንድንችል በንፅፅር ያቀረበልን
ወንድም ነው፡፡ ረጂም ጊዜ እንደወሰደበት ከጊዜም ከጉልበትም አዕምሮውንም ብዙ ማማጥ እንዳለ ነው
ያየሁት ይሄ እንግዲህ ወጣቶች በተለይ ለወጣቶች የኤፌሶንን መልዕክት ይሄን ይሄን ድርሳን አግኝተው ቢያነቡት
አበረታታለሁኝ ለምንድነው እንደዚህ የምለው ወንድማችን አዲያምሰገድ የኤፌሶን መልዕክት እንዳስቀመጠው
እኔም እንዳነበብኩት በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ መሠረታዊ ትምህርቶች ከድነት ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ኢየሱስ
ምፅዓት የተንፀባረቁበት መጽሐፍ ነው ስለዚህ ለአዲስ ክርስቲያን ወጣት፣ በብስለት ጉዞ ውስጥ ነኝ ለሚልም
ወጣት፣ አገልጋይ ነኝ ለሚልም ወጣት ለሁሉም እንዲበጅ ተደርጎ የተጻፈ መጽሐፍ ነው ይሄ የኤፌሶን መልዕክት
ላይ ያለው ጥናት ማለት ነው፡፡ እንደገና ደግሞ አንባቢን ሊያበረታታ በሚችል መልኩ ነው የተጻፈው፣ የተጻፈበት
የቋንቋው ይዘት ይሄ ምንድነው ነጮች ሪደር ፍሬንድሊ ወይም ደግሞ ከአንባቢ ጋር በቀላሉ ሊወዳጅ የሚችል
የሥነ ጽሑፍ ይዘት ነው ያየሁበት አንዴ ከጀመራችሁት እንዳታቋርጡ በሚያደርግ መልኩ ነው የተጻፈው ወጣቶች
ደግሞ በዚህ ሁኔታ የተጻፉ ድርሳናትን በቀላሉ አትራክትድ ሆነው ሊያነቡ እንደሚችሉ አስባለሁኝ፡፡ እንግዲህ ይሄ
በተለይ በደቀመዝሙርነት ሒደት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነው የሚያደርግላቸው ብዬ አምናለሁ፡፡
ለምንድነው ይሄ ደቀመዝሙር ማለት በእግዚአብሔር ቃል የሚያድግ በፀሎት የሚያድግ፣ ከቅዱሳን ጋር ደግሞ
ሕብረት የሚያደርግ እና ወንጌልን ደግሞ ለሌሎች የሚያዳርስ በእነኝህ አራት አቅጣጫዎች ላይ በደንብ እራሱን
አሹሎ የሚሄድ ወጣት ነው ደቀመዝሙር ወጣት ማለት፡፡
ስለዚህ እራስን በእግዚአብሔር ቃል ለመትከል የእግዚአብሔር ቃል ምቹ የሆነና በቂ ጊዜ ሰጥቶ ቁጭ
ብሎ የእግዚአብሔርን ቃል ማጥናት ያስፈልጋል እንግዲህ መጽሐፍ ቅዱስ ሁላችንም እንደምናውቀው ከበድ
በሚል ቋንቋዎች የዚህን ዘመን ወጣት በማይመጥኑ ወይም ደግሞ ለመረዳት በሚያስቸግሩ የቀድሞ
አማርኛዎች የተጻፉ ናቸው በአብዛኛው ኢቭን በአዲስ መልኩ ተተርጉሟል የምንለው መጽሐፍ በአብዛኛው
እንግዲህ የመጽሐፍ ቅዱስ ይዘት ራሱ ከሁለት ሺሕ ዓመታት በፊት የነበሩ ታሪኮችን የሚያትት ስለሆነ ያለ አጋዥ
መጽሐፍ ለመረዳት አስቸጋሪ ነው መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ አጋዥ መጽሐፍት በተለይ ደግሞ ወንድማችን
አዲያምሰገድ እንደጻፈው ዓይነት በቀላሉ መልዕክቱን ለመረዳት የሚያግዙ ናቸው፡፡ ስለዚህ ይሄን መጽሐፍ ከጎን
አድርገው መጽሐፍ ቅዱሳቸውን የተለየ ጊዜ ሰጥተው እንዲያጠኑ እራሳቸውን በዚህ እንዲያንፁ እንዲያጎለብቱ
ለወጣቶች መምከር እፈልጋለሁኝ፡፡ ይሄን ሲያደርጉ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው እየበሰሉ፣ እግዚአብሔርን
በማወቅ እያደጉ በመንፈሳዊ ፍሬዎችም እየጎለበቱ በመንፈሳዊ ፀጋ ስጦታዎችንም በአግባቡ ለመጠቀም
እንዲረዳቸው በክርስቶስ ኢየሱስ ያገኙትን የድነት ነፃነትንም በደንብ በእውቀት መሠረት እንዲያስይዙ ሊረዳ
የሚችል መጽሐፍ እንደሆነ እረዳለሁ፡፡ ግን ይሄን ለማለት እፈልጋለሁኝ፡፡ እንግዲህ የእኛ ይሄ ያየሁት የማጥኛ
መጽሐፍ በእኛ አገር ብዙ የማጥኚያ መጽሐፍቶችን ለማየት ዕድሉን አግኝቻለሁኝ በተለያዩ ሰዎች የተጻፉ
አብዛኞቹ በኢትዮጵያዊ የተጻፉ አይደሉም፡፡ ደግሞም በእኛ ቋንቋ የተጻፉ አይደሉም ማለት በአማርኛ የተጻፉ
አይደሉም፣ እንግሊዝኛን ማንበብ የሚችል ወጣት ውስን ወጣት ነው ይሄ በአማርኛ መቅረቡ በገጠርም
በከተማም ያለውን የተማረ ያልተማረ የሚባለውንም ወጣት ሁሉንም ወጣት አድሬስ በሚያደርግ ሁኔታ ነው
የቀረበው ስለዚህ በእኛ አገር ሰው መጽሐፉ በጣም አስደናቂ ነው ብዬ መመስከር እችላለሁኝ፡፡
እንግዲህ ከዚህ ቀጥዬ ማንሳት የምፈልገው ወንድማችን አዲያምሰገድ የፌሶንን መልዕክት ብቻ
አይደለም ያዘጋጀው ሌሎች በርካታ መጽሐፍቶችን ጽፏል እኔ በተለይ ለረጅም ጊዜ በፌስቡክ ላይክ አድርጌ
እከታተለው ነበር፡፡ አንዳንድ ትምህርቶቹን በቪዲዮም አይቻቸዋለሁ መጽሐፍቶቹንም አግኝቻቸዋሐሁ በሶፍት
ኮፒ ያሉ መጽሐፍቶችም አሉ እና ይሄም ከፍተኛ ጥረቱን ጊዜ በጣም ውድ በሆነበት የባዕድ ምድር እየኖረ ይሄን
ካበረከተልን እንግዲህ ሰዎች በተለያየ መልኩ ይሄንን አገልግሎት መደገፍ አለባቸው ብዬ አስባለሁኝ፣
አምናለሁኝ አንዱ በእሱ አገልግሎት መስመር ውስጥ የሙያ ድጋፍ ሊያደርጉ የሚችሉ፣ የአስተምህሮት ድጋፍ
ሊያደርጉ የሚችሉ በርካታ ሰዎች እንዳሉ አስባለሁኝ በኢትዮጵያ ምድር ካሉ ጥቂት ከማይባሉ የሥነ መለኮት
ኮሌጆች ተመርቀው ብዙ አቅም ያላቸው አገልጋዮች እንዳሉ አውቃለሁ ግን እንደሱ የመጻፍ አንጀቱ የሌላቸው
ሊሆኑ ይችላሉ ስለዚህ ከእሱ አንዱ የሚማሩት መጻፍን ውስጣቸው ያለውን ነገር መጽሐፍን ጽፎ ማለፍ ለጋሲን
መተው ነውና እንደሱ ይሄንን ፈለግ መከተል አለባቸው አስባለሁ እንግዲህ ፈለጉን መከተል አንዱ ከጎኑ ሆኖ
በዚህ ሥራ ውስጥ አብሮ እሱ የሚጽፋቸውን መጽሐፍት በመተየብ ሊሆን ይችላል፣ ሐሳብ በማዳበር ሊሆን
ይችላል፣ ሐሳብ በማዋጣት ሊሆን ይችላል ከዚያም አልፎ የአገልግሎት መጽሐፍን ማሳተም ከፍተኛ የሆነ
የገንዘብ አቅም ይጠይቃል፡፡ በገንዘብም ድጋፍ በማድረግ፣ በሕትመት ሒደት ውስጥም ድጋፍ በማድረግ ከጎን
ሆኖ አይዞህ ማለትም ትልቅ ድጋፍ ነው፣ ከጎንህ አለን ማለትም ትልቅ ድጋፍ ነው፤ ይሄን ሁሉም ክርስቲያናዊ
ወገን ሁሉም ቤተክርስቲያናት ከጎኑ ሆነው ሊረዱት እንደሚገባ ላሳስብ እወዳለሁ በተለይ ደግሞ የቃለ ሕይወት
ወጣቶች ይሄን መጽሐፍት አግኝተው እንዲጠቀሙ፣ ወንድማችን አዲያምሰገድ በዩቲዩብ፣ በፌስቡክ ላይ
ብዙዎችን ለመድረስ በርካታ ተከታዮች እንዳሉት አውቃለሁኝ እና በዚያም የእርሱን አገልግሎት በመጠቀም
መደገፍ እንደሚገባቸው በሐሳብ ማበረታታት እንደሚገባቸው፣ በገንዘብም፣ በቁሳዊ ድጋፍም አብረውት
መሆን እንደሚገባቸው ወንድማዊ ምክሬን መለገሰ እፈልጋለሁኝ ጌታ ይባርካችሁ!